የጡት ማጥባት ምክር

 
በልጅሽ እድገት የመጀመሪያዎቹ 1000 ቀናት ጡትማጥባት በጣም አስፈላጊ ተግባር ነው፡፡ የአለም የጤናድርጅት ህፃናት እስከ ስድስት ወር ድረስ ጡት ብቻ መጥባትእንዳለባቸው አጥብቆ ያስገነዝባል፡፡ ከስድስት ወር በኋላምቢሆን እስከ 2 ዓመት ቢቻል ከዚያም በላይ ህፃናት ጡትመጥባት እንዳለባቸው ድርጅቱ በአንክሮ ያሣሥባል፡፡ልጅሽ ጡት ሲጠባ የሚያስፈልገውን ንጥረ-ነገር በሙሉከአንቺ ስለሚያገኝ ህይወቱን በግሩም ሁኔታ ይጀምረዋል፡፡ጡት ማጥባት ለአንቺም ሆነ ለልጅሽ ዘለቄታዊ ጠቀሜታአለው፡፡ ስታጠቢ የሚከተሉትን ምግቦች እና ንጥረ- ነገሮችየያዙ ምግቦችን መመገብ ጠቀሜታው እጅግ የጎላ ነው፡፡
 
 
 
 
 
 

ጡት መጥባት ልጅሽን እንደሚጠቅመው ታውቂያለሽን?

 
 • የጡት ወተት በቀላሉ ከልጅሽ ሰውነት ጋር ይዋሀዳል፡፡ለልጅሽ አስፈላጊየሆኑትን ፕሮቲን፣ ካርቦኃይድሬትና ስብን በተፈላጊው መጠን የያዘ ምግብነው፡፡
 • የጡት ወተት፣ የልጅሽ ሰውነት በሽታ አምጪ ተዋህስያንን የመከላከልአቅሙን የሚያጎለብቱ አንቲቦዲስ/በሽታ ተከላካይ/ የተባሉ ንጥረነገሮች አሉት፡፡ በተጨማሪም ጀርምን መከላከል የሚችሉ ንጥረ ነገሮችምአሉት፡፡
 • ልጅሽን እስከ ስድስት ወር ወይም ከዚያ በላይ ጡት ካጠባሽው፣ በወደፊትህይወቱ ክብደቱ ከሚገባው በላይ የመሆንና የመወፈር እድሉ አናሳ ነው፡፡
 • ልጅሽ መጥባት የሚኖርበትን ያህል ካጠባሽው ጤናማ ጥርስ ያድግለታል፡፡ጥርሶቹ የመበስበስ እድላቸው በጣም አነስተኛ ነው፡
 • ጡት በሚገባ ከጠባ በወደፊት ህይወቱ በደም ግፊት፣ በኮሌስትሮልናበሁለተኛው አይነት የስኳር በሽታ የመጠቃት እድሉ አነስተኛ ይሆናል፡፡
 • ጡት የጠቡ ህፃናት አስር ዓመት ሲሞላቸው በሂሳብ፣ በማንበብና በመፃፍጡት ካልጠቡ ህፃናት የተሻሉ ይሆናሉ፡፡
 • ማጥባት ላንቺም ቢሆን ጥሩ ነው፡፡
 • ልጅሽ በሚጠባበት እድሜ ጡትሽ ሁሌም ወተት ይኖረዋል፡፡ ስለዚህ፣ልጅሽን ይዘሽ ወጣ ማለት ብትፈልጊ ስለሚበላው ሳትጨነቂ ይዘሽውመውጣት ትችያለሽ፡፡
 • ጡት ማጥባት ከማረጥ በኋላ ሊፈጠር የሚችለውን በጡትና በማህፀንካንሰር የመጠቃት እድልን ይቀንሳል፡፡
 • ማጥባት ተፈጥሮአዊ የሆነ የክብደት መቀነሻ ዘዴ ነው፡፡ በቀን ከ500-600 ካሎሪ ስለሚቃጠል ካጠባሽ ክብደትሽ የመቀነስ እድል አለው፡፡

 
 
 
 
 
 
 
 
 
 

ስታጠቢ መመገብ ያለብሽ ምን አይነት ምግቦችን ነው? መመገብ የማይኖርብሽስ?

 
 • ስታጠቢ ጤናማና የተመጣጠነ ምግብ መመገብ አለብሽ፡፡ የጥራጥሬ ምግቦች፣ቀይ ሥጋ፣የዶሮ ስጋ፣የዓሣ ሥጋ፣አተር እና ስብ የሌላቸው የወተት ውጤቶች፣ወተት እና የተለያዩአትክልትና ፍራፍሬዎች የተመጣጠነ ንጥረ-ምግብን ለሰውነታችን ከሚሰጡ ምግቦችውስጥ ናቸው፡፡አመጋገብሽ የተጠና ይሁን፡፡ ለሰውነትሽ ትክክለኛውን ንጥረ-ምግቦች የሚሰጡሽን ምግቦችተመገቢ፡፡ ምግብሽ የሚከተሉትን የምግብ አይነቶች ያካተተ ይሁን፡፡
 • በቂ ፕሮቲን ያላቸው እንደ ቀይ ስጋ፣ ዓሣ፣ ሰርዲን፣ እንቁላል፣ ባቄላ፣ ምስርየመሣሠሉትን ገንቢ ምግቦች መመገብ አለብሽ፡፡ በቪታሚንና በሚኒራል የተጠናከሩየቁርስ ምግቦችን፣ አረንጓዴ ቅጣላ-ቅጠሎችንም በበቂ ሁኔታ መመገብ አለብሽ፡፡እነዚህ ምግቦች ለልጅሽ አእምሮና አካላዊ እድገት ወሳኝ ሚና አላቸውና፡፡
 • ቅባት የበዛባቸውና በቅባት የተጠበሱ ምግቦች ያላቸው የጠቃሚ ንጥረ-ምግብ ይዘትአነስተኛ ነው፡፡ የስብና የካሎሪ መጠናቸውም ከሚያስፈልግሽ እጅግ የበዛ ነው፡፡ ስለዚህአትመገቢያቸው፡፡
 • ማጥባት ውሀ ጥምን ሊያስከትል ይችላል፡፡ በዛ ያለ ውሀ ጠጪ፡፡ቢያንስ በቀን 8ብርጭቆ/2 ሊትር/ ውሀ ጠጪ፡፡
 • ስታጠቢ፣ ሰውነትሽ ከመደበኛው ተጨማሪ የሆነ ከ300-500 ካሎሪ ይጠቀማል፡፡ይህ መጠን ከ1 ሣንድዊች (300 ካሎሪ) ወይም ለአንድ ምግብ የሚሆን የፓስታ ስጎ(ወደ 500 ካሎሪ) ጋር ይመጣጠናል፡፡ ታዲያስ? ስለዚህ ለሁለት ሰው የሚሆን ምግብመመገብ ያስፈልግሻል!አትዘናጊ! አስታውሺ! መጠነኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴመስራት ጉልበት ይሠጥሻል፡፡ ስሜትሽንም ያነቃቃዋል፡፡
አትዘናጊ! አስታውሺ! መጠነኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መስራት ጉልበት ይሠጥሻል፡፡ ስሜትሽንም ያነቃቃዋል፡፡

 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 

ካፌይን ያላቸውን መጠጦችን ቀንሺ፡፡ ካፌይን ከሌለው ቅጠል ላይ ከተዘጋጀ ሻይቅጠል የሚፈላ ሻይ መጠጣት አንዱ አማራጭ ነው፡፡

 
ማርገዝ ከፈለግሽና የእርግዝና ጊዜሽን በእቅድ ለመምራት ከወሰንሽ ከእርግዝና በፊት በአኗኗርሽ ላይ አዎንታዊ ለውጥ ማድረግ አለብሽ፡፡ ለውጥ ለማድ ረ ግ ጤናማ የ ሆ ነ የ አ ኗ ኗ ር ዘ ዴ ን መቀ የ ስ
አለብሽ፡፡ከእርግዝና በኋላም ደግሞ እቅድሽን በትጋት መተግበር ይኖርብሻል፡ ማርገዝ ስትወስኚ ክብደትሽ መሆን ባለበት ኪሎ ላይ ከሆነና የምትመገቢው ምግብ የተመጣጠነ ከሆነ እርግዝናው በጥሩ ሁኔታ ይጀምራል፡፡ ይህ መግቢያ ለማርገዝ ስታስቢና ከወለድሽ በኋላ ላሉት ሁለት ዓመታት ልጅሽን እንዴት መመገብ እንደሚኖርብሽ ሀሳብ
ይሰጥሻልና አንብቢው፡፡