የእርግዝና ምክር

 
 
 
 
 

ለእርጉዝ እናቶች ጠቃሚ ሀሳብ

 
በልጅሽ እድገት የመጀመሪያዎቹ 1000 ቀናት ጡትማጥባት በጣም አስፈላጊ ተግባር ነው፡፡ የአለም የጤናድርጅት ህፃናት እስከ ስድስት ወር ድረስ ጡት ብቻ መጥባትእንዳለባቸው አጥብቆ ያስገነዝባል፡፡ ከስድስት ወር በኋላምቢሆን እስከ 2 ዓመት ቢቻል ከዚያም በላይ ህፃናት ጡትመጥባት እንዳለባቸው ድርጅቱ በአንክሮ ያሣሥባል፡፡ልጅሽ ጡት ሲጠባ የሚያስፈልገውን ንጥረ-ነገር በሙሉከአንቺ ስለሚያገኝ ህይወቱን በግሩም ሁኔታ ይጀምረዋል፡፡ጡት ማጥባት ለአንቺም ሆነ ለልጅሽ ዘለቄታዊ ጠቀሜታአለው፡፡ ስታጠቢ የሚከተሉትን ምግቦች እና ንጥረ- ነገሮችየያዙ ምግቦችን መመገብ ጠቀሜታው እጅግ የጎላ ነው፡፡
 
 
ጥቆማ 1÷ ኦሜጋ-3
በሳምንት አንዴ ወይም ሁለቴ በምግብሽ ውስጥ ዓሣ ለማካተት ሞክሪ፡፡ በተለይ የዓሣ ዘይት ምንጭ የሆኑ ዓሣዎችን፡፡

ጥቆማ 2÷ተጨማሪ ንጥረ ነገሮች
በየቀኑ በቪታሚን ዲ የበለፀጉ ምግቦችን ተመገቢ፡፡ዓሣ፣ እንቁላል ወይም በቪታሚን ዲ ተጠናክሮ የተዘጋጀ ወተት ጠጪ፡፡ ለመጀመሪያዎቹ 12 የእርግዝና ሳምንታት ፎሊክ አሲድ በየቀኑ(400μg) ብትወስጂ መልካም ነው፡፡

ጥቆማ 3÷ ካልሲየም
በቀን ሶስት ጊዜ ወተትና የወተት ውጤቶችን በምግብሽ ውስጥ ለማካተት ሞክሪ፡፡ በየቀኑ
ሶስት ጊዜ ወተት፣ አይብና እርጎ ጥቂት-ጥቂት ውሰጂ፡፡

ጥቆማ 4÷ ብረት(Iron)
በብረት ማዕድን የበለፀጉ ምግቦችን በቀን 2 ጊዜ በምግብሽ ውስጥ ለማካተት ሞክሪ፡፡
በብረት በበለፀጉ ምግቦች ውስጥ ቀይ ስጋ፣ የዶሮ ስጋ፣ እንቁላል፣ ባቄላና አረንጓዴ ቅጠላ ቅጠሎች ይካተታሉ፡፡

ጥቆማ 5÷ ጣፋጮች
ጣፋጭ የበዛባቸውን ምግቦችና መጠጦች አልፎ-አልፎ በተለየ አጋጣሚ ብቻ ተመገቢ፡፡

ጥቆማ 6÷ አትክልትናፍራፍሬ
በቀን ውስጥ ለ 3 ጊዜ ያህል ከምግብሽ ጋር አትክልትና ፍራፍሬ ለመመገብ ሞክሪ፡፡

  • ኦሜጋ 3፡ የዘይት ምንጭ የሆኑ የዓሣ ሥጋዎችን በምግብሽ ውስጥ ለማካተት ሞክሪ፡፡
  • በቀን1ጊዜ እንደ ዓሣ፣ እንቁላል፣ ቪታሚን ዲ ታክሎበት የተዘጋጀ ወተት የመሳሰሉትን በቪታሚን ዲ የበለፀጉ ምግቦችን ለመመገብ ሞክሪ፡ልጅሽ የመጀመሪያ ዓመት የልደት በዓሉን እስኪያከብር ድረስ የቪታሚን ዲ ጠብታ ቢወሰድ ወይም ከጸሀይ ብርሀን ቢያገኝ ይመረጣል ፡፡
  • ልጅሽ በተለይ የመጀመሪያ ዓመት የልደት በዓሉን እስኪያከብር ድረስ ቪታሚን ዲ ከፀሀይ ብርሃን ማግኘት አለበት።
  • ቢያንስ በቀን 8 ብርጭቆ (2 ሊትር) ውሀ ጠጪ፡፡ በመደበኛው የምግብ ሠዓትና የመክሰስ ሠዓት የተመጣጠነ ምግብ መመገብሽን እርግጠኛ ሁኚ፡፡