የመጀመሪያ ምግቦች

 
 

ጠጣር ምግብ ከመጀመራቸው ቀደም ብለው ያሉት ጊዜያት

 
እንደ ጤና ባለሙያዎቹ ገለፃ ህፃናት ጠጣር ምግብ መጀመሪያቸውከስድስት እስከ ስድስት ወር ተኩል ባለው ጊዜ ውስጥ ነው፡፡አንዳንድ ህፃናት ግን ቀደም ብለው ጠጣር ምግብ የመመገብ ፍላጎትያሳያሉ፡፡ቀደም ብለሽ ጠጣር ምግብ መጀመር ሥታስቢ መጀመሪያ ሀኪምወይም የጤና ባለሞያ አማክሪ፡፡ለልጅሽ ተጨማሪ ምግብ መስጠት ስትጀምሪ፣ በቀን አንድ ጊዜበአንድ የሻይ ማንኪያ ሩዝ ወይም ጓጓላ የሌለው ቀጭን የአትክልትድልህ ጀምሪ፡፡ በዚህ ወቅት የልጅሽን የንጥረ-ምግብ ፍላጎትየሚያሟላው ወተት ነው፡፡ያም ሆኖ ቀደም ብለው የተጀመሩት እነዚህየመጀመሪያ ምግቦች፤ የልጅሽ የወደፊት የአመጋገብ ባህልየሚገነባባቸው መሠረቶች መሆናቸውን መገንዘብ ይኖርብሻል፡፡ የዚህወቅት ምግብ በልጅሽ አመጋገብ ባህል ላይ ወሳኝ የሆነ ከፍተኛ ተፅዕኖስለሚያስከትል በስኬት ልትወጪው ይገባል፡፡
 

ተስማሚ ምግቦች (ማካተት ያለብሽ ምግቦች)

 
 • ሩዝ፦ ከውሃ፣ ከጡት ወተት ወይም ከተዘጋጀ የህፃናት ወተት ጋር ተደባልቆ
 • መሀከለኛ ጣዕም ያላቸው በሹካ የተዳመጡ አትክልቶች፡፡ መጀመሪያ በድንች ጀምሪ፡፡ ከዚያ ካሮት፤ ፓርስኒኘ ወይም ጎደሬ / ሩታባጋ// ልታዘጋጂለት ትቺያለሽ፡፡
 • መካከለኛና የተፈጥሮ ጣፋጭነቱን የያዘ ከፖም ወይም ከፒር የተሰራ የአትክልት ድልህ፡፡
ልጅሽን የምትመግቢያቸው ብዙ አይነት ምግቦች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ቀስ- በቀስና በትክክለኛው ጊዜ ምግቦቹን አለማምጂው፡፡
በዚህ እድሜ ያሉ ሕፃናት መመገብ የማይኖርባቸው ምግቦች፡-
 • ቅመማ-ቅመም የበዛበት ምግብ
 • ጨው፡- በዚህ እድሜ ጨው የህፃናትን ኩላሊት ስራ ስለሚያበዛበት የልጅሽን ምግብ በጨው አታጣፍጪ፡፡
 • ደርቀው የተቀመጡ ምግቦች፣ ስጋና በቅመም የተዘጋጀ
 • የላም ወተት አታጠጪው ፡-(ጡት አጥቢው ወይም የተዘጋጀ የሕፃናት ወተት ብቻ አጠጪው፡፡)
 • እንደ ስንዴ፣ አጃ፣ ገብስ የመሳሰሉ ግሉቲን የተባለው ውሁድ ያላቸው ምግቦች፡፡ የታሸገ ምግብ ከገዛሽ ማሸጊያው ላይ የተፃፈውን አንብቢ፡፡
 • እንቁላል
 • ሥጋ፣ ዓሳ፣ የዶሮ ስጋ፣ ኦቾሎኒ፣ ማርና ስብ ያላቸው ምግቦች
ሲትረስ ፍሬዎች (ኮምጤ ፍሬዎች) ብርቱካን፣ መንደሪን፣
የመሳሰሉት ፤ ቤሪ ፍራፍሬዎች (ወይናስተኔ ፍሬዎች) ወይን፣ የመሳሰሉት ፍሬዎችን የአንዳንድ ህፃናት ሰውነት አይቀበለውም፡፡ (አለርጂክ ይሆናሉ፡፡)
አዋቂዎች የሚወዱዋቸው ምግቦች፣ ሆኖም እነዚህ ምግቦች በዚህ እድሜ ላሉ ህፃናት አይሰጡም፡፡
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 

ሩዝ

 
 • ከ1-3 የሻይ ማንኪያ ሩዝ
 • 3 የቡና ሲኒ የጡት ወተት ወይም የተዘጋጀ የህጻናት ወተት
አዘገጃጀት፡
 1. ሩዙን ከላይ በአማራጭነት ከቀረቡት ወተቶች ከአንዱ ጋር ደባልቆ በደንብማብሰል
 2. በደንብ መብሰሉን ከአረጋገጡ በኋላ መፍጨት
 3. መብረዱን ከአረጋገጡ በኋላ በትንሽ ማንኪያ መመገብ።ልጆች ተጨማሪ ምግብ በሚጀምሩባቸው ጥቂት ሳምንታት ውስጥ ሩዝ ዋናምግቡ ሊሆን ይችላል፡፡
 
 
 
 

የአትክልት ድልህ

 
1 ምግብ ይወጣዋል፡፡
1 አነስተኛ ድንች
1 አነስተኛ ካሮት
1 የቡና ሲኒ የእናት ጡት ወተት ወይም የተዘጋጀ የህጻናት ወተት
አዘገጃጀት:-ድንችና ካሮቱን ቀቅሎ ማብሰልመብሰሉን ከአረጋገጡ በሁኋላ ከወተቱ ጋር ደባልቆ መፍጨት ወይምማንኪያ በመጠቀም ማላምመብረዱን ከአረጋገጡ በኋላ በትንሽ ማንኪያ መመገብ።
 
 
 
 

የፍራፍሬ ድልህ

 
1 ምግብ ይወጣዋል፡፡
ግብአቶች
ሩብ የተቀቀለ አፕል ወይም ፒር
ግማሽ የቡና ሲኒ የእናት ጡት ወተት ወይም የተዘጋጀ የህጻናትወተት
አዘገጃጀት
የተቀቀለውን አፕል/ፒር ከወተቱ ጋር እየደባለቁ በማንኪያማላምበማንኪያ መመገብ።