2 ምግብ ይወጣዋል፡፡
ግብአቶች- 1 አነስተኛ ካሮት
- 1 አነስተኛ ድንች
- 2 ግንድ የብሮኮሊ ግንጣይ
- 1 የሻይ ማንኪያ ዘይት
- 3 የቡና ሲኒ የእናት ጡት ወተት ወይም የተዘጋጀ የህጻናት ወተት
አሠራር- ካሮቱን ፍቆ፣ ድንቹን ልጦ፤ በትንንሹ ከትፎ ማጠብ እና ድስት ውስጥ ከወተቱጋር ደባልቆ መጣድ
- የብሮኮሊውን ግንጣይና ጎመኑን በትንንሹ ከትፎ ማጠብና ድስቱ ውስጥ ከድንችእና ካሮቱ ጋር አንድ ላይ ማብሰል
- በደንብ መብሰላቸውን ከአረጋገጥን በኋላ፤ በመፍጫ ወይም በማንኪያ ማላም
- የላመውን ውህድ ድስት ላይ ገልብጠን ዘይቱን መጨመርና ለ10 ደቂቃማንተክተክ
- ጥቂት በጎድጓዳ ሰሃን አውጥቶ መመገብ።
- የተረፈ ካለ በ24 ሰዓት ውስጥ አሙቆ መመገብ።
ለማቀዝቀዝ የሚመች ምግብ ነው፡፡
ጥቆማ፡- ቀጠን እንዲል ከተፈለገ ጥቂት የእናት ጡት ወተት ወይም የተዘጋጀ የህፃናትወተት በመጨመር ቀጠን አድርጎ መመገብ።