2 ምግብ ይወጣል፡፡
ግብአቶች- 2 ቲማቲም
- 1 ቀይ ሽንኩርት
- 1 ድንች
- 4 እንጉዳይ (ነጭ)
- 2 የቡና ሲኒ የተፈጨ ቀይ ሥጋ
- 4 የቡና ሲኒ ውሃ
- 1 የሻይ ማንኪያ ካቻአፕ
አሠራር- ቲማቲሙን አጥቦ በፈላ ውሃ ውስጥ ገንፈል ማድረግ እና ልጦ እስኪልም ድረስ መክተፍ
- ሽንኩርቱን እና ድንቹን ልጦ አጥቦ በደቃቁ መክተፍ፡፡
- እንጉዳዩን አጥቦበስሱ መሰንጠቅ
- ስጋውን አጋም እስኪመስል ድረስ ብቻውን በመጥበሻ ላይ መጥበስ
- ቲማቲሙን፣ ድንቹን፣ እንጉዳዩንና ሽንኩርቱን ጨምሮ ለ10 ደቂቃእስኪዋሃዱ ድረስ በደንብ ማብሰል
- ውሀውን እና ካቻፑን ጨምሮ እስኪፈላ መጠበቅ፡፡ ሲፈላ እሳቱን ቀንሶስጋው እና አትክልቶቹ እስኪበስሉ ድረስ 40 ደቂቃ ማንተክተክ
- የሚያስፈልገን የልመት ደረጃ ድረስ በመፍጫ ማሽን መፍጨት
- በጎድጓዳ ሰሃን ቀንሶ በማንኪያ መመገብ
- የተረፈ ካለ በ24 ሠዓት ውስጥ አሙቆ መመገብ።
ለማቀዝቀዝ ምቹ ምግብ ነው፡፡
2 ምግብ ይወጣዋል፡፡
ግብአቶች- 1 ድንች
- 1 ካሮት
- በትንሹ የተቆረጠ ዱባ
- 1 ስር የባሮ ሽንኩርት
- 1 የቡና ሲኒ የተፈጨ የጥጃ ሥጋወይም ለስላሳ የበሬ ሥጋ
- 3 የቡና ሲኒ ውሃ
አሠራር- ካሮቱን፣ ድንቹን እና ዱባውን ልጦ አጥቦ በትንንሹ መክተፍ፡፡ባሮሽንኩርቱን እኩል ሰንጥቆ በደንብ አለቅልቆ በትንንሹ መክተፍ፡፡አትክልቶቹን በሙሉ መጥበሻ ላይ አድርጎ ማብሰል፡፡
- የተፈጨውን ሥጋ ከአትክልቶቹ ጋር አዋህዶ ማብሰልውሃውን ጨምሮ ለ30 ደቂቃ ማንተክተክ
- መብሰሉን ካረጋገጥን በኋላ በሚፈለገው የልስላሴ መጠን መፍጨት
- በጎድጓዳ ሰሃን ላይ ቀንሶ መመገብ
- የተረፈ ካለ በ24 ሠዓት ውስጥ አሙቆ መመገብ።
ለማቀዝቀዝ የሚመች ምግብ ነው፡፡
1-2 ምግብ ይወጣዋል፡፡
ግብአቶች- 1 የቡና ሲኒ የተፈጨ የጥጃ ሥጋ
- 2 ካሮት
- አንድ እጅ የሚሆን ፎሰሊያ
- 1 ድንች
- 3 የቡና ሲኒ ውሃ
አሠራር- ድንቹንና ካሮቱን ልጦና አጥቦ መክተፍ፣ ፎሶልያውን ቀንጥሶ ማለቅለቅ
- ሥጋውን፣ ድንቹንና ካሮቱን ከውሀ ጋር በድስት ውስጥ ከቶ ማብሰል፡፡
- ሲፈላ እሳቱን ቀንሶ 30 ደቂቃ ማንተክተክ
- ፎሶልያውን ጨምሮ ለተጨማሪ 10 ደቂቃ ከአትክልቶቹ ጋር ማብሰል
- መብሰሉን ካረጋገጥን በኋላ በሚያስፈልገው የልስላሴ መጠን መፍጨት
- በጎድጓዳ ሰሃን ላይ አውጥቶ መመገብ።
ለማቀዝቀዝ ምቹ የሆነ ምግብ ነው፡፡