ተጨማሪ ምክሮች

 
 
 
 
 

ማጥባት ከመጀመርሽ በፊት ማወቅ የሚገባሽ

 

ልጅሽ ጡት መጥባት አለበት! ጡት ማጥባት ለልጅሽ የህይወት ስንቅ ነው፡፡

 
ስታጠቢ፣ በህይወትሽ ከምትሰሪያቸው ስራዎች በሙሉ በጣም ጠቃሚውንና ከፍተኛውን አስፈላጊ ሥራ እየሰራሽ ነው፡፡ ስታጥቢ፣ ለልጅሽ ምርጥ የሆነውን ተፈጥሮአዊ ምግብእየመገብሽ ነው፡፡ ስለዚህ ራስሽን ተንከባከቢ! በዚህ ልዩ ጊዜ መመገብ ያለብሽን የተመጣጠነ ምግብ በሙሉ መመገብሽን እርግጠኛ ሁኚ፡፡ልጅሽ በአካልም ሆነ በስሜት ድንቅ በሆነ ሁኔታ ህይወቱን መጀመሩን እርግጠኛ ለመሆን፤ በመጀመርዎቹ 1000 ቀናቶች ብዛት ያላቸው ምርጫዎችን መምረጥና ውሳኔዎችንመወሰን ይኖርብሻል፡፡ እነዚህ 1000 ቀናት ከእርግዝና እስከ ሁለት ዓመት እድሜ ያሉት ጊዜያት ናቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ዋናዉና ትክክለኛ ውሣኔ ልጅሽን ለማጥባት መወሰንሽ ነው፡፡ይህን መፅሀፍ የምታነቢው እያጠባሽ ከሆነ፤ ማጥባት ለአንቺና ለልጅሽ የሚሰጣችሁን ጥቅሞች ተረድተሻል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ይህንን በልጅሽ ህይወት ውስጥ ልዩና አስደሣችየሆነውን ጊዜ በደስታ እያሣለፍሽ ነው ማለት ነው፡፡ይሁንና፣ ፤ማርገዝ ካቀድሽ ወይም እርጉዝ ከሆንሽና ስለማጥባት ተጨማሪ መረጃዎችን የምትፈልጊ ከሆነ ይህ የምታነቢው መፅሀፍ ትክክለኛው የመረጃ ምንጭሽ ነው፡፡ ጡትማጥባት ለልጅሽ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ የጡት ወተት ተፈጥሮ ያዘጋጀችለትን ንጥረ-ምግቦች ይሰጠዋል፡፡ ቀንም ሆነ ማታ በፈለገበት ጊዜ ሊጠባ ይችላል፡፡ አንቺም ለጡትሽ ወተትገንዘብ አትከፍይም፡፡ ያም ሆኖ የጡት ወተት ጥቅም ከምቾትና ከገንዘብ ያለፈ ነው፡፡ ጡት ማጥባትም ሆነ መጥባት ለአንቺና ለልጅሽ ጤና ከፍተኛ ጥቅም አለው፡፡ ልጅሽ ጡትመጥባት ካቆመም በኋላ ጥቅሙ ይቀጥላል፡፡