ማሙሽ ድክ-ድክ ሲል

 
 
 
 
 
 

ሼፐርድስ ፓይ

 
ግብአቶች

 • 2 ትንሽ ሽንኩርት
 • 2 ሲኒ የተፈጨ ቀይ ስጋ
 • 2 የሻይ ማንኪያ የስንዴ ዱቄት
 • 2 ማንኪያ የቲማቲም ድልህ
 • 1 ደበርጃን
 • 2 ካሮት
 • 1 መካከለኛ ድንች
 • 1 የቡና ሲኒ ወተት
 • 1 ማንኪያ የገበታ ቅቤ

አሠራር

 1. ቀደም ብሎ ድስቱን ማጋል፤ ሽንኩርቱን ልጦ ፣አጥቦ በትናንሹ መክተፍና ከስጋውጋር ድስት ውስጥ ከትቶ ስጋው ቡናማ መልክ እስኪይዝ ድረስ መጥበስ
 2. እያማሰሉ ዱቄቱን መጨመር፡፡ቀጥሎም የቲማቲም ድልሁን እና ውሃ ጨምሮ ለ30ደቂቃ ማብሰል
 3. የተዘጋጀውን ደበርጃን፣ ድንች እና ካሮት ልጦ፤ አጥቦ በትንንሹ መክተፍ እና ቀቅሎ ማብሰል
 4. የበሰለውን የአትክልት ውህድ ከወተቱና ከግማሹ ቅቤ ጋር አዋህዶ በማንኪያ ማላም
 5. የበሰለውን ስጋ ኦቨን ውስጥ ሊገባ በሚችል ትንንሽ ጎድጓዳ ሰሃን ላይ መገልበጥ እናበቅቤ የላመውን የአትክልት ውህድ ስጋው ላይ በማንኪያ እየቀነሱ ከስጋው ላይ መደልደል
 6. ኦቨን ውስጥ ከትቶ ለ 30 ደቂቃ መጋገር
 7. ሲቀዘቅዝ በመመገቢያ ሰሃን ላይ ቀንሰን መመገብ።
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 

ፍሬንች ቶስት

 
2 ምግብ ይወጣዋል፡፡

ግብአቶች

 • 2 የተቆራረጠ (እስላይስ) ዳቦ
 • 2 እንቁላል
 • ግማሽ ሲኒ ወተት
 • 1 የሾርባ ማንኪያ የገበታ ቅቤ
 • ግማሽ የሻይ ማንኪያ የተወቀጠ ቀረፋ

አሠራር

 1. ሰፋ ባለ ጎድጓዳ ሰሃን ላይ እንቁላሉን በማንኪያ በደንብ መምታት፣እንቁላሉ ላይ ቀረፋውን እና ወተቱን ጨምሮ እንደገና በማንኪያ በደንብ መምታት
 2. መጥበሻውን እሳት ላይ አድርጎ ማጋል፤ ቅቤውን ማቅለጥ
 3. ዳቦውን የእንቁላሉ ውህድ ውስጥ ጨምሮ በውህዱ ማራስ እና መጥበሻላይ አድርጎ በአነስተኛ ሙቀት እያገላበጡ መጥበስ
 4. ትንሽ አቀዝቅዞ መመገብ።
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 

ባለ ቅርፅ ፒዛ

 
1 ምግብ ይወጣዋል፡፡

ግብአቶች

 • አንድ ፒዛ ሊሰራ የሚችል የተቦካ ሊጥ
 • 3 ማንኪያ የቲማቲም ድልህ
 • 2 ቲማቲሞች
 • 3 የቡና ሲኒ የተፈረፈረ ቺዝ
 • 1 የፈረንጅ ቃሪያ
 • 1 ካሮት
 • 1 የቡና ሲኒ የተፈጨ ስጋ
አሠራር

 1. በቅድሚያ ኦቨኑን ማጋል፡፡ የተዘጋጀውን ሊጥ በማማሰያ ወይም በመዳመጫ ክብቅርጽ አስይዞ መዳመጥ እና የፒዛ መጋገርያ ትሪው ላይ አድርጎ የቲማቲም ድልሁን መቀባት፡፡ ቲማቲሞቹን ከትፎ ከቺዙ እና ከስጋው ጋር ፒዛው ላይ መበተን
 2. ኦቨኑ ውስጥ ከቶ ቺዙ እስኪነፋ ድረስ ለ15 ደቂቃ ማብሰል
 3. ፒዛው እያበሰለ ቃሪያውን ለሁለት ሰንጥቆ ፍሬውን በማዉጣት በደቃቁ መክተፍ፤ካሮቱን አጥቦና ልጦ መፈቅፈቅ
 4. የደቀቀውን ቃሪያ እና የተፈቀፈቀውን ካሮት ፒዛው ላይ መበተን
 5. አቀዝቅዞ መመገብ።