ማርገዝ ከፈለግሽና የእርግዝና ጊዜሽን በእቅድ ለመምራት ከወሰንሽከእርግዝና በፊት በአኗኗርሽ ላይ አዎንታዊ ለውጥ ማድረግ አለብሽ፡፡ለውጥ ለማድ ረ ግ ጤናማ የ ሆ ነ የ አ ኗ ኗ ር ዘ ዴ ን መቀ የ ስአለብሽ፡፡ከእርግዝና በኋላም ደግሞ እቅድሽን በትጋት መተግበርይኖርብሻል፡ ማርገዝ ስትወስኚ ክብደትሽ መሆን ባለበት ኪሎ ላይከሆነና የምትመገቢው ምግብ የተመጣጠነ ከሆነ እርግዝናው በጥሩሁኔታ ይጀምራል፡፡ ይህ መግቢያ ለማርገዝ ስታስቢና ከወለድሽ በኋላላሉት ሁለት ዓመታት ልጅሽን እንዴት መመገብ እንደሚኖርብሽ ሀሳብይሰጥሻልና አንብቢው፡፡
እንኳን ደስ አለሽ! በጣም አስደሳች የሆነን ጉዞ አንድ ብለሽጀምረሻል፡፡ እርግጥ ነው፣ በ40ኛው ሳምንት መጨረሻ ላይ እንግዳልጅሽን ለመቀበል እንደጓጓሽ ጥርጥር የለውም፡፡ እነዚህ 40ሳምንታት ከ1000 ቀናት ጉዞሽ የመጀመሪያዎቹን 270 ቀናትንይወክላሉ፡፡ የ1000 ቀን ጉዞሽ ልጅሽ 2 ዓመት እስኪሞላው ድረስየምትጓዢው ጉዞ ነው፡፡ ወቅቱ ለልጅሽ አካላዊና አእምሮአዊ እድገትከፍተኛ ጥቅም የሚሰጡ አስፈላጊ እርምጃዎችን የምትወስጂበትትክክለኛ ጊዜ ነው፡፡በነዚህ ሁለት ዓመታት ልጅሽ ለወደፊት እድገቱዳግም በማይታይ ሁኔታ አእምሮውና አካሉ በፍጥነት ያድጋል፡፡አካላዊና አእምሮአዊ እድገቱ ህይወቱን ሙሉ የሚዘልቅ ጤናናበደስታ የተሞላ ህይወት ያጎናፅፈዋል፡፡ይህን ፈጣን አካላዊና አእምሮአዊ እድገት የሚደግፍ የአመጋገብዘዴን ይጠቁምሻልና ይህን መፅሀፍ በጥንቃቄ አንብቢ፡፡ አሁንም ሆነለወደፊት ህይወቱ ለልጅሽ ጤናማ አካላዊና አእምሮአዊ እድገትየተመጣጠነ ምግብ አስፈላጊ ነው፡፡ስለዚህ በእርግዝናሽ ወቅት የምትመገቢው ምግቦች የሚከተሉትንንጥረ ነገሮች ቢያካትት መልካም ነው፡፡
በየቀኑ ቪታሚን ዲ (5 µg) ለመውሰድ ሞክሪ፡፡ በቪታሚን ዲ የበለፀጉ ምግቦችን ተመገቢ፡፡ ዓሣ፣ እንቁላል ወይም በቪታሚን ዲ ተጠናክሮ የተዘጋጀ ወተት ጠጪ፡፡ ለመጀመሪያዎቹ 12 የእርግዝና ሳምንታት ፎሊክ አሲድ (400 µg) በየቀኑ ብትወስጂ መልካም ነው፡፡
ካልሲየምበቀን ሶስት ጊዜ ወተትና የወተት ውጤቶችን በምግብሽ ውስጥ ለማካተት ሞክሪ፡፡ በየቀኑ ወተት፣ አይብና እርጎ ጥቂት-ጥቂት ሶስት ጊዜ ውሰጂ፡፡
ብረት (Iron)በብረት ማዕድን የበለፀጉ ምግቦችን በቀን 2 ጊዜ በምግብሽ ውስጥ ለማካተት ሞክሪ፡፡ በብረት የበለፀጉ ምግቦች ውስጥ ቀይ ስጋ፣ የዶሮ ስጋ፣ እንቁላል፣ ባቄላና አረንጓዴ ቅጠላ ቅጠሎች ይካተታሉ፡፡
ጣፋጮችጣፋጭ የበዛባቸውን ምግቦችና መጠጦች አልፎ-አልፎ በተለየ አጋጣሚ ብቻ ተመገቢ፡፡ ለምሳሌ በሳምንት ሁለቴ፡፡
አትክልትና ፍራፍሬበቀን ውስጥ ለ5 ጊዜ ያህል ከምግብሽ ጋር አትክልትና ፍራ-ፍራፍሬ ለመመገብ ሞክሪ፡፡