1 ምግብ ይወጣዋል፡፡
ግብአቶች- 1 እንቁላል
- 1 የሻይ ማንኪያ የተፈጨ ስኳር
- 1 የሻይ ማንኪያ ቫኔላ ፍሌቨር
- 2-3 ስኒ የእናት ጡት ወተት ወይም የተዘጋጀ የህፃናት ወተት
አሠራር
- ቀደም ብሎ ኦቨኑን ማጋል፡፡
- እንቁላሉን፣ ስኳሩንና ቫኔላ ፍሌቨሩን በጎድጓዳሰሃን ውስጥ ከቶ በሹካ/በማንኪያ/ እየመቱ ማዋሃድ
- ወተቱን በትንሽ ድስት ውስጥ ጨምሮ ሞቅ ማድረግ
- ሞቅ ያለውን ወተት ቀስ እያሉ ድብልቁ ውስጥ እየጨመሩ ማዋሃድ፡፡
- ጓጓላውእስኪጠፋ ድረስ እያማሰሉ በደንብ ማዋሃድ
- ድብልቁን ኦቨን ውስጥ ሊገባ በሚችል ጎድጓዳ ሰሃኖች ውስጥ አጥልሎ በማብሰያ ትሪ ላይ ማስቀመጥ፡፡
- ሰሃኖቹ ግማሽ ድረስ የሚሆን የፈላ ውሀማብሰያ ትሪው ላይ መጨመር ድብልቁ እስኪጠጥር ድረስ በምድጃ ውስጥ ከ15-20 ደቂቃ ማብሰል
- እስኪቀዘቅዝ ጠብቆ መመገብ።
ለማቀዝቀዝ የሚመች ምግብ ነው፡፡
5 ዳቦ ይወጣዋል፡፡
ግብአቶች- ግማሽ ሲኒ ለማለስለሻ የሚሆን ዘይት
- 3 የቡና ሲኒ የዳቦ ዱቄት
- 1 የሻይ ማንኪያ ጃም/ማርሜላት/
- 1 እንቁላል አስኳል
አሠራር- የዳቦ መጋገሪያውን ምጣድ ቀደም ብለን በዘይት አሽተን ለኩሰን ማጋል፤ዱቄቱን በጎድጓዳ ሰሃን ውስጥ ጨምሮ በውሃ እያዋህዱ ማቡካት
- ጓጓላው እስኪጠፋና ተለጣጭ እስኪሆን ድረስ ለ5 ደቂቃ በደንብ ማቡካት
- ከተቦካው ሊጥ ላይ እየቀነስን በምንፈልገው መልኩ ቅርጽ እየሰጠን የጋለው ምጣድ ላይ መደርደር እና ምጣዱን ማጥፋት
- የተዘጋጀውን ጃም እና የእንቁላል አስኳል በማንኪያ ማዋሃድ እና ውህዱንየዳቦ ሊጦቹን በስሱ መቀባት፡፡ ኩፍ እስኪልም መጠበቅ
- ሊጡ ኩፍ ሲል፤ ምጣዱን መልሰን ለኩሰን ከ10-15 ደቂቃ ድረስማብሰል
- የበሰለውን ዳቦ መመገብ ።
8 ኬኮች ይወጣዋል፡፡
ግብአቶች- 4 ማንኪያ የገበታ ቅቤ
- 2 ስኒ የተፈጨ ስኳር
- 4 የቡና ሲኒ ዱቄት
- 1 እንቁላል
አሠራር
- ቀደም ብሎ ኦቨኑን ማጋል፡፡ ትናንሽ የማፍን መጋገሪያ ወረቀቶችን በመጋገርያትሪው ላይ መደርደር
- የኬኩን መስሪያ ጥሬ እቃዎች በጎድጓዳ ሰሃን ውስጥ ከቶ ጓጓላው እስኪጠፋድረስ ማቡካት
- ድብልቁን የመጋገሪያ ወረቀቶቹ ውስጥ እኩል አካፍሎ ኦቨን ውስጥ መክተት፤በደንብ ንፍት ብለዉ ወርቃማ መልክ እስከሚያመጡ ድረስ ማብሰል
- ሲበስል አቀዝቅዞ በወተት ወይም ብቻውን መመገብ።
- የተረፈውን ማቀዝቀዣ ውስጥ ማስቀመጥ።