ግብአቶች
- 2 ትንሽ ሽንኩርት
- 2 ሲኒ የተፈጨ ቀይ ስጋ
- 2 የሻይ ማንኪያ የስንዴ ዱቄት
- 2 ማንኪያ የቲማቲም ድልህ
- 1 ደበርጃን
- 2 ካሮት
- 1 መካከለኛ ድንች
- 1 የቡና ሲኒ ወተት
- 1 ማንኪያ የገበታ ቅቤ
አሠራር- ቀደም ብሎ ድስቱን ማጋል፤ ሽንኩርቱን ልጦ ፣አጥቦ በትናንሹ መክተፍና ከስጋውጋር ድስት ውስጥ ከትቶ ስጋው ቡናማ መልክ እስኪይዝ ድረስ መጥበስ
- እያማሰሉ ዱቄቱን መጨመር፡፡ቀጥሎም የቲማቲም ድልሁን እና ውሃ ጨምሮ ለ30ደቂቃ ማብሰል
- የተዘጋጀውን ደበርጃን፣ ድንች እና ካሮት ልጦ፤ አጥቦ በትንንሹ መክተፍ እና ቀቅሎ ማብሰል
- የበሰለውን የአትክልት ውህድ ከወተቱና ከግማሹ ቅቤ ጋር አዋህዶ በማንኪያ ማላም
- የበሰለውን ስጋ ኦቨን ውስጥ ሊገባ በሚችል ትንንሽ ጎድጓዳ ሰሃን ላይ መገልበጥ እናበቅቤ የላመውን የአትክልት ውህድ ስጋው ላይ በማንኪያ እየቀነሱ ከስጋው ላይ መደልደል
- ኦቨን ውስጥ ከትቶ ለ 30 ደቂቃ መጋገር
- ሲቀዘቅዝ በመመገቢያ ሰሃን ላይ ቀንሰን መመገብ።
2 ምግብ ይወጣዋል፡፡
ግብአቶች- 2 የተቆራረጠ (እስላይስ) ዳቦ
- 2 እንቁላል
- ግማሽ ሲኒ ወተት
- 1 የሾርባ ማንኪያ የገበታ ቅቤ
- ግማሽ የሻይ ማንኪያ የተወቀጠ ቀረፋ
አሠራር- ሰፋ ባለ ጎድጓዳ ሰሃን ላይ እንቁላሉን በማንኪያ በደንብ መምታት፣እንቁላሉ ላይ ቀረፋውን እና ወተቱን ጨምሮ እንደገና በማንኪያ በደንብ መምታት
- መጥበሻውን እሳት ላይ አድርጎ ማጋል፤ ቅቤውን ማቅለጥ
- ዳቦውን የእንቁላሉ ውህድ ውስጥ ጨምሮ በውህዱ ማራስ እና መጥበሻላይ አድርጎ በአነስተኛ ሙቀት እያገላበጡ መጥበስ
- ትንሽ አቀዝቅዞ መመገብ።
1 ምግብ ይወጣዋል፡፡
ግብአቶች- አንድ ፒዛ ሊሰራ የሚችል የተቦካ ሊጥ
- 3 ማንኪያ የቲማቲም ድልህ
- 2 ቲማቲሞች
- 3 የቡና ሲኒ የተፈረፈረ ቺዝ
- 1 የፈረንጅ ቃሪያ
- 1 ካሮት
- 1 የቡና ሲኒ የተፈጨ ስጋ
አሠራር- በቅድሚያ ኦቨኑን ማጋል፡፡ የተዘጋጀውን ሊጥ በማማሰያ ወይም በመዳመጫ ክብቅርጽ አስይዞ መዳመጥ እና የፒዛ መጋገርያ ትሪው ላይ አድርጎ የቲማቲም ድልሁን መቀባት፡፡ ቲማቲሞቹን ከትፎ ከቺዙ እና ከስጋው ጋር ፒዛው ላይ መበተን
- ኦቨኑ ውስጥ ከቶ ቺዙ እስኪነፋ ድረስ ለ15 ደቂቃ ማብሰል
- ፒዛው እያበሰለ ቃሪያውን ለሁለት ሰንጥቆ ፍሬውን በማዉጣት በደቃቁ መክተፍ፤ካሮቱን አጥቦና ልጦ መፈቅፈቅ
- የደቀቀውን ቃሪያ እና የተፈቀፈቀውን ካሮት ፒዛው ላይ መበተን
- አቀዝቅዞ መመገብ።